Welcome message

ወደዚህ የጡመራ መድረክ እንኳን ደህና መጡ፡፡ ለሚሰጡኝ ማናቸውም አስተያየት እግዚአብሔር ይስጥልኝ፡፡
Welcome to my blog. Your feedback, comments and suggessions are most appreciated.



Sunday, November 6, 2011

ባለ ፩ መክሊት



በህልሜ ህልም አለምኩ
ካዛውንቱ አባቴ ካጠገቡ ነበርኩ


በህልሜ


መክሊት ሰጠኝ አርበኛው አባቴ
ይቺው ናት ያለችኝ አንዲቷ ጥሪቴ
ሲሆን አትርፍባት አደራ በሞቴ
በደም ነው የቆየች ተከስክሶ አጥንቴ
በህልሜ ህልም አለምኩ
ከአንዱ ስወጣ ሌላው ውስጥ ሰጠምኩ



ካንደኛው ህልሜ ነቅቼ ስንጠራራ
በአንዲቷ መክሊቴ ጀመርኳ ላቅራራ


የጀግና ልጅ ጀግና
ምን ይጎድለኝና
ሌላው ሁሉ ከንቱ ብቻ ልሁን ጤና
መክሊቴን ዘርዝሬ እኖራለሁ ገና


ደስታዩ ልክ አጥቶ ድንገት ብንን ብል
አይኖቼን ጨፈንኩኝ ህልሜ እንዲቀጥል


እንደው ላይሆንልኝ ጊዜዬ ባከነ
ከእውነት መጋፈጥ ግድ ሊሆን ሆነ


እውነታው


እንኳን በመክሊቷ አትርፌ ልነግድ
እርሷኑ ቀብሬ ላደራው ሳልሰጥ ግድ
እበደር ጀመረ ከቀጣዩ ትውልድ


በባደ ሜደ.


የዓድዋ ድል ቦክቶ
ዳቦ ላይሆን ከቶ


ለቅኝ አለመንበርከክ
ወጥ ሳይሆን ሽሮ ክክ
               
ስለ ፫ሺህ ዘመን መጎረር
የ፶ አመት ልደት ሳይከበር
እያሉ አብረውን በሽታና ችጋር

ጀመርኩዋ ማማረር.


ወይ ኢትዮጵያዬ መሄጃ ያጣሁብሽ ቤቴ
ትሆኝኛለሽ ስል መመኪያ መክሊቴ
ወኔዬን ትሰልቢው ሳይደክም ጉልበቴ


የረሃብ የችግር የጦርነት አውራ
በሰላም በፍትህ የሃገሮች ውራ


በኔ ልፈር ባንቺ
ኧረ መላ ምቺ


ግና..


አልዘልቀውም እንጂ ምክንያቱን ዘርዝሬ
ምንጩ ግን ግልጽ ነው ጥንትም ሆነ ዛሬ


የቅናት ልጆቹ በቀል ምቀኝነት
የነሱም ዝርያ ከንቱ ደም መቃባት


የስንፍና አጎት መቁረጥ እምነት ተስፋ
ታዲያ ብልጽግና በየት በኩል ይስፋፋ


ውስጣችንን ሞልቶት ሐሜት ጥርጣሬ
ቤት ይቆም ይመስል ማገር ሆኖት ወሬ


እግዚአብሄርን መፍራት ሳያልፍ ከከንፈር
ምን ያለ ትድግና እንጠብቅ ተአምር


መደምደሚያ……


ቢመሽም ቀኑ ጭላንጭል ያለ ባይመስልም
መኖር ስላለብኝ ፍለጋው አያልቅም
መክሊቴን እስካገኝ እስካለሁ በአለም


መሬቱም ልቤ ነው መክሊቱ እውነት
ቆፍሬ እንደቀበርኩ ቆፍሬ ላገኛት
ቃል ገባሁ ለራሴ እንድወጣ ሃርነት


 ኅዳር ፲፯ ቀን ፲፱፺፰  . .

2 comments:

  1. I didn't know U are bloging until I red ur comment on Daniel Kibrets Blog.

    I checked ur blog after that it is realy good though u don't have many followers/viewers it is ok. The one thing I noticed is most of ur writings are in Engilish I wonder why is it because u cann't write in Amharic or u don't want to?

    By the way I want to express my feeling about the accident I'm realy sorry about it and happy that u are Ok. May God protect u and ur family and nice to see u on blog (I was ur student at St. Marry's University College).

    ReplyDelete
  2. ሰላምታዬን በማስቀደም፡ ምስጋናዬን ላስከትል፡፡ በቋንቋዬ በጣም እኮራለሁ፡ ልጠቀምበትም እወዳለሁ፡፡ ግና በኮምፒውተር ለመጻፍ እጅግ ይቸግረኛል፡ ከችሎታ ማነስ። ይህቺን እንኳ ለመጻፍ ብዙ ጊዜ ፈጀሁ፡፡ ወደፊት እጥራለሁ፡፡ ግን ማን ልበል? መንገር ከወደዱ ማለት ነው። የቅ/ማ/ዩ/ኮ የጥቂት ጊዜ የማስተማር ቆይታዬን በጥሩ ትዝታ አስበዋለሁ። ብዙም ተምሬበታለሁ፡፡

    እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

    ReplyDelete