መኖር አለመኖር…
አርብ በማለዳ ለሥራ ስንገባ
ኖረን ስለማኖር ለመስራት በአላማ
አንዱ ሰው ያለሆነ ሰው በተቃርኖ ሃሳብ
አጥፍቶ ለመጥፋት ተዘጋጅቶ ከልብ
መኪናውን ሞልቶ ተቀጣጣዬ ቦምብ
በሩን እየጣሰ ፍጥነቱን ጨምሮ
ካሰበበት ደርሶ ሳይራራ አምርሮ
ቦምቡን ቢያፈነዳው ቆርጦ በህይወቱ
ጀነት እንዲገባ ስላመነበቱ
ልክ እንዳሳመኑት የመንፈስ አባቱ
በዚያች ትንሽ ቅጽበት የጊዜ እራፊ
የንጹሃን ስጋ ሰውነት ትራፊ
ተቆራሬጦ ወደቀ እንዳንዳንች ርጋፊ
እኔስ ግራ ገባኝ የዚህ ነገር ጉዱ
ጀነት የሚገባው በየት ይሆኔ መንገዱ
ለመድረስ ቢታሰብ ከተመኟት ጀነት
እንዴት ያሸልማል ነፍሰ ገዳይነት
ምድሩን ሲኦል አድርጎ መኖር በሰማያት
አንድ…ሁለት…ሶስት
ወይ መኖር ወይ መሞት
ከሁለት አንዱ ነው
ሊሆን የነበረው
አምላክ ባያስቀረው
ሞትን ተው ባይለው
አእምሮዬን አዞ እግሬን ባያስኬደው
ከአሳንሰሩ አሬቆ ከእሳት ባያወጣው
መሬት ተደፍቼ ጀመርኩኝ ጸሎት
ገና ሳልዘጋጅ እንዳልሄድ ሰማይ ቤት
‘ላገር ወገን ሳልበጅ ሳልመልስ ብድራት
ባክህ ማረኝ ጌታ የሁለቱ ሕጻናት
ከስጋና ከነፍስ ከሞትም የሞት ሞት
በቀኝህ የሚያቆም ሳዬኖረኝ ትሩፋት
እባክህ አትጥራኝ አምላከ ምህረት
ለሁሉም ጊዜ አለው እንዳለ ሶሎሞን
አሁን አልወስድህም ሌላ ቀጠሮ አለን
ብሎ አለፈኝ አምላክ ከመአት አዳነን፡፡
ልጆቼ አቅርቡ ዝማሬ ማኅሌታይ
ለቤዛ ኩሉ አለም ለአምላክ አዶናይ
ተግታችሁ ጸልዩ ፍሬያችሁን እንድናይ
ዕጣን ሽቶውንም አቅርቡለት መባዕ
ከሃጢያት እርቀን ንስሃ እንድንገባ
ማርልን ነፍሳቱን ወዳንተ የመጡትን
በአጽናኝ መልዓክ ጠብቅ ቤተሰባቸውን
ቁስላቸውን ፈውሽ የአምላክ አናት
ህሊኛቸው ይዳን ካሳለፉት መዓት፡፡
መታሰቢያነቱ፡
በነሐሴ ፳ ቀን ፪ሺህ፫ ዓም፡ ዕለተ ዓርብ ከጠዋቱ ፬ ሰዓት ከ፳ ደቂቃ፡ አቡጃ፡ ናይጄሪያ፡ የተ.መ.ድ መ/ቤት፡ ላይ በተፈጸመው የአጥፍቶ መጥፋት አደጋ በሕይወት ለተለዩኝ ባልደረቦቼ ይሁን፡፡
ያጌት፡ ተጻፈ ነሃሴ ፴ ቀን ፪ሺህ፫ ዓም. በኢትዮጴያ አየር መንገድ ወደጆሃንስበርግ፡ ደቡብ አፍሪካ ጉዞ ላይ፡፡
Betam libn yemineka gitim new. Awo, lemotut nefs yimar, lebetesebochachew metsnanatin yistachew, egnanm yetebeken amlak misgana yigbaw. AMEN!
ReplyDeleteyouo are lucky that you can put what you feel in rhyme. Well, I LOVE the poem............
ReplyDelete