Welcome message

ወደዚህ የጡመራ መድረክ እንኳን ደህና መጡ፡፡ ለሚሰጡኝ ማናቸውም አስተያየት እግዚአብሔር ይስጥልኝ፡፡
Welcome to my blog. Your feedback, comments and suggessions are most appreciated.



Showing posts with label ግጥሞች (Poems). Show all posts
Showing posts with label ግጥሞች (Poems). Show all posts

Sunday, November 6, 2011

ባለ ፩ መክሊት



በህልሜ ህልም አለምኩ
ካዛውንቱ አባቴ ካጠገቡ ነበርኩ


በህልሜ


መክሊት ሰጠኝ አርበኛው አባቴ
ይቺው ናት ያለችኝ አንዲቷ ጥሪቴ
ሲሆን አትርፍባት አደራ በሞቴ
በደም ነው የቆየች ተከስክሶ አጥንቴ
በህልሜ ህልም አለምኩ
ከአንዱ ስወጣ ሌላው ውስጥ ሰጠምኩ


Friday, September 16, 2011

አጭሯ ጸሎት

አጭሯ ጸሎት


በሰላም አውለኝ የሚሏት ጸሎት
ጥቂት ትመስላለች ሲቆጥሯት በቃላት
ትርጉሟ ሊገባን ሰላም የጠፋ ዕለት


ያጌት፡ ተጻፈ ነሃሴ ፳፱ ቀን ፪ሺህ፫ ዓም.  በኢትዮጴያ አየር መንገድ ወደጆሃንስበርግ፡  ደቡብ አፍሪካ ጉዞ ላይ፡፡
(Inspired by the deadly suicide bombing of the UN building in Abuja, occurred on 26 August 2011)

Tuesday, September 13, 2011

መኖር አለመኖር…

መኖር አለመኖር…
አርብ በማለዳ ለሥራ ስንገባ
ኖረን ስለማኖር ለመስራት በአላማ

አንዱ ሰው ያለሆነ ሰው በተቃርኖ ሃሳብ
አጥፍቶ ለመጥፋት ተዘጋጅቶ ከልብ
መኪናውን ሞልቶ ተቀጣጣዬ ቦምብ

በሩን እየጣሰ ፍጥነቱን ጨምሮ
ካሰበበት ደርሶ ሳይራራ አምርሮ